Sem ena Werk ~ Bini Lasta



Sem ena Werk ~ Bini Lasta 

New Ethiopian Music 2018 

(Official Video) 
ሰም እና ወርቅ  


ህብር ተሞልቶ የነገሰ በታሪክ ማማ ላይ

መለስ ብዬ ሳልጎበኘው ማንነቴን ሳላይ

ለሃገሬ ሰው ባይተዋር ለታሪኬ እንግዳ
በኖርኩበት ባደኩበት የኔ ባልኩት ጓዳ


እንደራሱ ሆ ያልቻለ መሰረቱ ያጣ

ለሰው ክብር ልክበር የሚል ከሩቁ በመጣ


እረ ናናዬ ናናዬ ... መደማመጥ ጠፍቶት ሁሉም በራስ ወሬ

እረ ናናዬ ናናዬ ... ታላቅ እንደነበርን እንዴት ልየው ዞሬ
እረ ናናዬ ናናዬ ... ትልቅ በሆነበት ትንሽ ነኝ ሰው ካለ
እረ ናናዬ ናናዬ ... ጻድቅ አይባልም እውነት ስለጣለ


እረ ናናዬ ናናዬ እረ እማማዬ እማማዬ

የሰም እና ወርቅ ምድር ነሽ
ለካ አላውቅሽም ኢትዮጵያዬ (2X)


ግእዝን ብታውቀው ገዳም ብታጠና

ለታላቁ ምስል ልቦናህ ቢቀና


ካለፈው መማሪያ ካልጠፋባት ሃገር

ጅምሩ ባዶ ነው ከባዶ መጀመር


በል ሁን እንዳገርህ ልሁን እንደሃገሬ

በተውሶ ዛፍ ላይ ላታፈራ ፍሬ
እረ እንደምን አለህ
አለማወቄ ሃገሬ ቆጨኝ ለራሴ (4X)