ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ

ከዳዑድ ኢብሳ ኦነግ ጋር ከዓመታት በፊት በአስመራ የተለያዩት ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ ቲም ለማን ተቀላቀሉ::

የኦሮሚያ አንድነትና ነፃነት ግንባር መሪ ብርጋዴር ጀነራል ከማል ከዳኡድ ኢብሳ ኦነግ ጋር ከተለያዩ በኋላ ከኤርትራ ወጥተው በኡጋንዳ እንደቆዩ ይነገራል::

"የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች የትጥቅ ትግል ፋሽን ያለፈበት በመሆኑ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ወደ ሀገር ግቡ" በሚል የቀረበውን የዶ/ር ዓብይ ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የነበሩት ጀነራል ከማል ቲም ለማን በመቀላቀል የኦሮሚያ ፀጥታና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ሹመት አግኝተዋል::

በብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሚያ አንድነትና ነፃነት ግንባር ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ኦዴፓን ይቀላቀላል ተብሎ በሰፊው ሲነገር የነበረ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ድርጅቱ ዶ/ር ዓብይና ለማ መገርሳ ከሚመሩት ኦዴፓ ጋር ይቀላቀል አይቀላቀል አልታወቀም፡፡

ነገር ግን ጀነራል ከማል ቲም ለማን ተቀላቅለው ይህን ትልቅ ሹመት አግኝተዋል:: ለጀነራል ከማል ገልቹ የተሰጠው ሹመት በተለይም የዳኡድ ኢብሳን ኦነግ እንደማያስደስት የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ::